ማሳሙኔ በላይ የኢትዮጵያዊው አርቲስት፣ መምህር እና የኢትዮጵያ-ጃፓን ባህልና ታሪክ ተመራማሪ፥ ብርሃኑ ታደሰ ገሰሰ የብዕር ስም ነው። የብዕር ስሙ የአንጋፋው ጃፓናዊ ሳሙራይ ዳቴ ማሳሙኔን ከኢትዮጵያዊው ጀግና በላይ ዘለቀ ጋር ያጣምራል። ስሙ ተዋጊዎቹ በሞት ፊት ያሳዩት መለኮታዊ ጀግንነት ቀይቶ፣ የአርቲስቱን የሰውን አእምሮ እና መንፈስ አንድ ለማድረግ  የሚጓዘውን ተልዕኮ ይወክላል።

 

ብርሃኑ ተወልዶ ያደገው በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ነው። ከሀገሩ ወጥቶ ካሳለፈው ህይወት እየወሰደ፣ ስራዎቹ በቋንቋ እና በማንነት መካከል ያለውን የተሳሰረ ግንኙነት ይዳስሳሉ። በአሁኑ ጊዜ አማርኛ(የአፍ መፍቻ) እና እንግሊዘኛ ቋንቋን ይናገራል። በቅርቡም ወደ ጃፓን ተጉዞ፣ ጃፓንኛ ቋንቋን በማጥናት እና ባህላዊ ተረቶችን በመጻፍ፣ የቋንቋ እና ስነ-ጽሁፍን መንፈሳዊ ትርጉም ለመመርመር እቅድ አለው።

 

ብርሃኑ የፈጠራ ጽሁፍ (በልብ-ወለድ) ማስተርስ ዲግሪ (፳፻፳፭) ከምዕራብ ኬንተኪ ዩንቨርስቲ እና የእንግሊዘኛ ስነ-ጽሁፍ መጀመሪያ ዲግሪ ከኬንየን ኮሌጅ (፳፻፳፩) ባለቤት ነው። 

Masamune Belay is the pen name of Birhanu Tadesse Gessese, an Ethiopian artist, educator, and Ethiopia-Japan history and culture researcher. The pen name combines the legendary Japanese samurai Date Masamune with the Ethiopian hero Belay Zeleke. It alchemizes the warriors’ poetic resilience in the face of death and symbolizes the artist’s mission to unite the human mind and spirit.

 

Birhanu was born and raised in Ethiopia's capital Addis Ababa. Drawing from his diasporic experiences, his works explore the entwined relationship between language and identity. He currently speaks Amharic, mother tongue, and English as second language. He plans to move to Japan to study Japanese and write ethnographic stories to research the spiritual meaning of language and literature.

 

Birhanu holds a Master of Fine Arts in Creative Writing (Fiction Emphasis) from Western Kentucky University (2025), and a Bachelor of Arts in English Literature from Kenyon College (2021).

正宗ベライは、エチオピアの芸術家、教育者、エチオピア-日本の歴史と文化の研究者であるビルハヌ・タデッセ・ゲセセの筆名です。この筆名は、伝説的な日本の侍・伊達政宗とエチオピアの英雄・ベライ・ゼレケを組み合わせたものです。それは、死に直面した戦士たちの詩的な回復力を錬金術のように表現し、芸術家の人間の心と精神を結びつける使命を象徴しています。

 

ビルハヌは、エチオピアの首都アディスアベバで生まれ育ちました。自身のディアスポラ(離散)体験を創作の源泉とし、その作品を通じて、言語とアイデンティティの密接に絡み合った関係性を探求しています。現在は母語であるアムハラ語に加え、第二言語として英語を話します。彼は今後、日本へ移住して日本語を習得し、言語や文学が持つ精神的な意味を研究するための民族誌的な物語を執筆していく計画です。

 

ビルハヌは、ウェスタン・ケンタッキー大学にてクリエイティブ・ライティング(フィクション専攻)の美術学修士号(2025)を、ケニオン・カレッジにて英文学の文学士号(2021)を取得しています。- Google Translation


ኪነ-ጥበብ ምንድን ነው?

What is art?

文学とは何ですか?

ኪነ-ጥበብ ጥበብን በተለያዩ መልኮች ያዘለ አገልግል ነው፤ ኪነ-ጥበበኛውን ከሰው ጋር በህይወት መንገድ ላይ አገናኝቶ፣ እውቀት እና ተሞክሮን እንደ ምግብ እና ውሀ የሚያለዋውጥ ነው። ኪነ-ጥበብን በየዓይነቱ መመገብ የራስን አዕምሮ እና መንፈስ በጥበብ ማነጽ ነው። ስለሆነም፣ በእውነተኛ ምንነቱ እና ተፈጥሮው፣ ኪነ-ጥበብ መንፈሳዊ ነው።

Art is a basket of wisdom contained in various forms. It brings an artist and a person together on life's path, and exchanges knowledge and experiences like food and water. Consuming art in its variety establishes one's mind and spirit in wisdom. Thus, in its essence and original nature, art is spiritual.

芸術とは、様々な形をとった「知恵の宝庫」です。それは人生という道のりにおいて芸術家と人々を結びつけ、まるで糧や水のように、互いの知識や経験を分かち合わせるものです。多様な芸術に触れることは、人の心と精神を知恵によって満たし、確かなものへと育みます。したがって、その本質や本来の性質において、芸術とは精神的なものなのです。- Google Translation


ምርምር ምንድን ነው?

What is research?

研究とは何ですか?

ምርምር የነገሮች ሁሉ መሰረት ነው። ደራሲዎች፣ የሃይማኖት ሊቃውንት፣ ሰዓሊዎች፣ ሳይንቲስቶች፣ መሃንዲሶች፣ መሪዎች፣ ኮከብ አስይዎች፣ ተማሪዎች፣ ሙዚቀኞች፣ እና ሌሎችም፥ የሚያተውሉትን ጉዳይ ከግምት ወደ እርግጥ እንዲመጣ የሚጓዙት መንገድ ነው።

 

ምርምር የፈጠራ ልጅም ወላጅም ነው። የፈጠራ ሃሳብ ከጥያቄ ተነስቶ፣ ወደ መልስ ማግኘት ሲሄድ፣ ምርምር ይወለዳል። ታዲያ መልስ ወይም መላምት ሲገኝ፥ ምርምሩ ደግሞ መልሶ ፈጠራውን ወደ ተግባር እንዲቀየር አድርጎ ይወልደዋል። ስለሆነም፣ ምርምር በውልደት እና እድገት እየታደሰ፣ ዘመን የሚሻገር፣ የስልጣኔ ፋኖስ ነው።

Research is the basis of things. It is a path on which writers, painters, scientists, engineers, religious leaders, astrologers, students, musicians, and others move their observations from guesswork to actual understanding.

 

Research is both the child and parent of creativity and innovation. When a creative idea goes from a state of questioning to an answer, research is born. Then, when an answer or resolution is achieved, the research in turn births the idea into something actionable and practical. Therefore, research is a timeless process endlessly renewed by its birth and growth, making it a lamp of civilization. 

研究は物事の基礎です。それは作家、画家、科学者、技術者、宗教指導者、占星術師、学生、音楽家などが、自らの観察を推測から実際の理解へと移す道です。

 

研究は創造性と革新の両方の子であり親でもあります。創造的なアイデアが疑問の状態から答えへと移るとき、研究が生まれます。そして、答えや解決が得られたとき、研究はそのアイデアを実行可能で実際的なものとして生み出します。したがって、研究は生まれと成長によって絶えず新たにされる時代を超えたプロセスであり、文明の灯となります。- Google Translation